Sunday, March 8, 2015

የወያኔ የቤት ስራ ክመስራት ይልቅ ወደ ትግላችን ማተኮር አንገብጋቢ ጉዳይ ነው

ሕወሓት/ኢሕአዴግ ላለፉት 24 አመታት ሃገርን እና ሕዝብን በማጭበርበር በጎሳ ፖለቲካ ወገንን በውጭና በውስጥ እያመሰ ይገኛል::ይህ የወያኔ የከፋፋይነት እና የዘረኝነት ፖሊሲ በራሱ ላይ እዳ ይዞበት እየመጣ መሆኑን በገሃድ እያየነው ነው::ወያኔ ስልጣኑን ለማስረዘም የተለያየ የማዘናጊያ ስልቶችን በመንደፍ ለለውጥ ሃይሎች የቤት ስራ በመስጠት አትኩሮትን ለመስረቅ እየተራወጠ ይገኛል::በልማት እና በተለያዩ የሃሰት ንግግሮች ሕዝቡን ወደ ትግሉ እንዳያተኩር በስፋት እየተራወጠ በወንበሩ ላይ ለመቆየት በሚያደርገው ጥረት ሃገር ወዳዶችን ለማዘናጋት እና ለማደናበር የሚደረገውን ጥረት ልንዋጋው የሚገባ እና የለውጥ ሃይል የሆነው ህዝብ ለታላቅ ድል እንዲበቃ ሚናችንን መጫወት ያለበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን::

በሃገር ቤት እና በውጪው አለም በተሰራጩ የወያኔ ሆዳም ካድሬዎች እና ቅጥረኞች የዘረኝነት የግንጠላ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ወዘተ ጉዳዮችን በፈጠራ ወሬ ሕዝብን አደናብሮ ከትግሉ ጋር የማይያያዙ እና ትግሉን የሚያዘናጉ አሊያም የሚያስረሱ ሲሻም የሚጎትቱ የውይይት ነጥቦችን በማንሳት ወደ ተነሳንበት አላማ እንዳንሄድ እና እንዳንገሰግስ አከራካሪ የቤት ስራዎችን በመፍጠር እኛ በተሰጠን የቤት ስራ ስንሽከረከር ወያኔ ስልጣኑን የሚጠግንበትን መንገድ ለመቀየስ እየሮጠ ነው::ይህንን በመረዳት ወያኔ የሚሰራውን የተንኮል ሴራ በመረዳት ከሚረጫቸው መርዞች በነጠንቀቅ ከፈጠራ አከራካሪ የቤት ስራዎች ሳንታለል/ሳንዘናጋ ወደ ትግላችን በማተኮር የትግሉ አውራ አላማ የሆነውን ወያኔን የመደምሰሱን ስራ ላይ ልንፈጥንበት እና ልናተኩርበት ይገባል::የወያኔ የቤት ስራ ከመስራት ይልቅ ወደ ትግላችን ማተኮር እና ስለ ትግላችን ብቻ መወያየት እና ለተግባራዊ ሂደት መስራት ችላ የማንለው ጉዳይ መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment