Friday, March 14, 2014

ሙሰኞችና “ሙሰኛው” ፀረ ሙስና

ናትናኤል ካብትይመር (ኦስሎ ኖርዌይ)
. . . . . . .የኢትዮጲያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የህዝብንና የመንግስትን ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል ክስ የመሰረተባቸውን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን  . . . . . . የኢቲቪ ዜና
. . . . . ጉድ ፈላ በቃ ቀጥሎ ሴትዮዋ ነች  . . . . . የዋህ ኢትዮጲያውያን
. . . . . . . እባካችሁ በጥቂት ሺህ ብሮች የወር ደሞዝ የህዝብ አገልጋይ ነን እያላችሁ የሰባት ሚሊዮን ብር መኪና አትንዱ . . . . .” አፈጉባኤው
. . . . . . .የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስናን በማጋለጥ ጋር በተያያዘ በታሸገ ውሃ ተመርዘው ነው የሞቱት መባሉን ባናረጋግጥም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በኦሮሚያ ክልል መንግስታዊ ስብሰባዎች የታሸገ ውሃ መቅረብ መቆሙን አውቀናል  . . . . . . ለስርዓቱ እጅግ የቀረቡ የመንግስት ጋዜጠኞች
ባለፈው ሰሞን ጥቂት የመንግስት ባለስልጣናት በሙስና ሰበብ ተብሎ ዘብጥያ ሲወርዱ የታሳሪዎች ቁጥር ከወትሮው ለየት በማለቱ ፀረ ሙስና ስራውን ጀመረ ብለው ተስፋ የጣሉ ኢትዮጲያውያን ጥቂት አልነበሩም። እንደው የህዝባችን የዋህነት ነው እንጂ ፀረ ሙስና ከተመሰረተ ጀምሮ አንድም ቀን እንደስሙ ስራውን ሰርቶ እንደማያውቅ ፣ ጥቅሙም ሌላ እንደሆን የታወቀ ነው። እንጂማ ገና ያኔ እነ አቶ ታምራት ላይኔ ፣ እነ አቶ አባተ ኪሾ የመሳሰሉት በሙስና ሰበብ ወደ እስር ሲወርዱ በህዝብ ገንዘብ ጠግበው የደለቡ የመንግስት ባለስልጣናትና አጋፋሪዎቻቸው የውስኪ ብርጭቆአችውን እያጋጩ ሲሳለቁ ማንም የነካቸው አልነበረም። ምክንያቱም ነገሩ ሌላ ነው። የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ለመንግስት የሚሰጠው ጥቅም ሌላ ነው።
ሁሌ ሳስበው የሚያስገርመኝ እንደ ህወሃት መንግስት የተለያዩ አለማቀፋዊ መሰረት ያላቸውን ህግጋትና ደንቦች ለራሱ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ እየሸነሸነ የሚያውል መንግስት ያለ አይመስለኝም።
የኢትዮጲያ ፀረ ሙስና ኮሚሽንን የህወሃት መንግስት ሲያያቸው ያላማሩትን ፣ የውስጥ ጉዱን የሚያወጡበት የመሰለውን የገዛ ባለስልጣናትና ሹመኞቹን ማስወገጃ አርጎ ይጠቀመዋል ፥
የፀረ ሽብር ህግን ህዝብ የወደዳቸውን ፣ አካሄዳቸው ያሰጋውን ፣ እውነትን ለህዝብ የሚያጋልጡትን ጋዜጠኞችንና አማራጭ የፖለቲካ ሃሳብ አመንጪ አካላትን ማስወገጃ አርጎ ይጠቀመዋል ፥
መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥን (Business Process Reengineering) የህወሃት ካድሬዎችንና በሲቪል ሰርቪስ በኢሃዴጋዊ አገዛዝ ያጠመቃቸውን ጆሮ ጠቢዎች በየመንግስት መስሪያ ቤቶች ለመሰግሰግ ይጠቀመዋል ፥
አገር አቀፍ የመረጃ ደህንነት ጥበቃ (National Information Network Security) ሲስተሙን የተለያዩ የዜና አውታሮችንና ድረ ገፆችን በሃገር ውስጥ እንዳይታዩ ለመዝጋትና አማራጭ የፖለቲካ ሃሳብ አመንጪ አካላትን መረጃ ለመበርበሪያ ይጠቀመዋል ፥
አንዳቸውም ለተፈጠሩበት ፍልስፍና በሃገራችን በአግባቡ ስራ ላይ ሲውሉ አይታዩም : ሌሎችም ብዙ አሉ።
“ኧረ ይሄ አሰራር መጥፎ ነው” ሲባል ዋናውን ጥያቄ ሆን ብሎ በማድበስበስ “ህጉን የገለበጥነው በቀጥታ ካደጉት ሃገራት ነው” ይባልና ያልተጠየቀው ይመለሳል።
“የለም የለም ህጉን አተረጓጎማችሁ ልክ አይደለም” የሚል ጫን ያለ ጠያቂ ሲመጣባቸው “መጠነኛ የአፈፃፀም ችግር ስላለ ነው በቅርቡ እንቀርፋለን” ይላሉ ከዛሬ ስንት አመት ጀምሮ። 
ወደ ዋናው ሃሳቤ የሙስና ጉዳይ ልመለስና በአንድ ወቅት ከአንድ ጋናዊ ጓደኛዬ ጋር ስለ አህጉራችን አፍሪካ መሪዎችና ባለስልጣናት መረን የወጣ ሙስናና ገንዘብ መውደድ ባህሪ ስንወያይ በማልረሳው መልኩ እንዲህ አለኝ
“የሚገርምህ በምሳሌ ባስረዳህ የአፍሪካ ሃገራት ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር በሃገራቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲወያዩ ‘. . የሚያስፈልገን ከሃምሳ ሚሊዮን ዶላር በላይ ነው ስለዚህ እነዚህን ሃገራት ብድርና እርዳታ እንጠይቃለን በተጨማሪም ከህዝቡ መዋጮ እንጠይቃለን . .’ ብለው ስብሰባውን ይቋጫሉ ነገር ግን ሁለቱም እያንዳንዳቸው ከመቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ በአውሮፓና አሜሪካ በሚገኙ ባንኮች በድብቅ እንዳስቀመጡ ይተዋወቃሉ።  መሪዎቻችን ከግለኝነትና ከስግብግብነት ካልወጡና ከነዚህም ችግሮች የፀዳ አመራር ካላገኘን ገና የአፍሪካችን መከራ ብዙ ነው” አለኝ።
እኔም የሃገሬ መንግስት ከቀበሌ ጀምሮ የሾማቸው ሹመኞችና ባለስልጣናት ፣ የሚነዷቸው መኪኖች ፣ የሚኖሩበት ውብ ቪላዎች ፣ ታማኝ ምስኪን የመንግስት ሰራተኞች ፣ እንደ ቁመናው ያላማረበት የፀረ ሙስና ኮሚሽን ህንፃ ፣ የኢቲቪ ሙስና ነክ ዜና በቅፅበት በአምሮዬ ውልብ ውልብ እያሉ አለፉ።
በኢትዮጲያ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ አነስተኛ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። በተያያዘም የመንግስት ባለስልጣናትና ሹመኞችም የመንግስት ሰራተኞች መሆናቸውንም እናውቃለን። ይህ ማለት ደግሞ የመንግስት ባለስልጣናትና ሹመኞች ደሞዛቸው ከመንግስት ሰራተኞች እኩል በመንግስት የደሞዝ እርከን መሰረት ነው ማለት ነው። ሌላው የመንግስት ሰራተኛ በኑሮ ውድነት ናላው ሲዞር ባለስልጣናቱ ግን ደሞዛቸው ስንት እንደሆነ እንኳን አያውቁትም ምክንያቱም የገንዘቡ መጠን የሚነዱትን የሚሊዮኖች ብር መኪና የቀናት ነዳጅ እንኳን አይሸፍንም ፥ ታዲያ ማወቁ ምን ያረግላቸዋል። 
ደሞዛቸው ትዝ የሚላቸውና ብዙ ግዜ በርካቶቻችንን የሚያስገርመንና በቁጭት ፈገግ የሚያስብለን የገቢ ማሰባሰቢያ ወይም ቴሌቶን ሲዘጋጅ “ክቡር ሚኒስትር እከሌ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ሰጥተዋል ሞቅ ያለ ጭብጨባ” ሲባል ወይም የሚንስትሮቹ ሚስቶች ምን ያህል ቆጥበው ፣ ለፓርቲያቸው አዋጥተው ፣ ተቸግረው ፣  ተቸጋግረው ፣ ልጆቻቸውን እንደሚያስተምሩ ሲያወሩ ነው።
ኧረ ይሄ ነገር ልክ አይደለም ሲባል ፥ “ሃገር ለማሸበር” ወይም “የጥላቻ ፖለቲካ” ይባላል። ሲጀመር ውል ያለው የፖለቲካ ስርዓት የህወሃት መንግስት የለውም ሲቀጥል . . . . . . . .ግድ የለው አሁን ከዋናው ርዕሴ አልውጣ።
በርካታ የመንግስት ሹመኞችና ባለስልጣናት ቢሮ እንደው እግር ጥሏችሁ ከሄዳችሁና ቀና ብላችሁ አስተውላችሁ ከሆነ በግርግዳቸው ላይ የለጠፏት ወረቀት “ታማኝነት ፣ ግልፅነት ፣ የህዝብ አገልጋይነት ፣ ቅንነት ፣ የመሳሰሉት ውብ ቃላቶች” በተርታ ተለጥፈው ይታያሉ ነገር ግን ዝቅ ብላችሁ የሹመኛውን ወይም የባለስልጣኑን ፊት ስትመለከቱት “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” የሚባለው አበው ለምግብ ይሁን ለህዝብ ገንዘብ በውል ሳይለዩ ያወረሱን ብሂል ሁለመናውን ወርሶት ታዩታላችሁ። ሹመኛና ባለስልጣን እየተፈራረቀ “ምነው በኔ ተጀመረ እንዴ” እየተባባለ ያችን ምስኪን ሃገር ይግጣል።
ሙስናና ንቅዘት በሃገር ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊም ሆነ ዲሞክራሲያዊ እድገት ላይ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ እጅግ ብዙ ነው። ስልጣንን መከታ በማድረግ የሚገኝ ገቢ መዘዝ የሃገርን ሃብት በማውደም ብቻ አያበቃም። የመንግስት ስልጣንና ሹመት ሃገርንና ህዝብን ማገልገል መሆኑ ይቀርና የቤተሰብ እንዲሁም የዘመድ አዝማድ የገቢ ምንጭና ህልውና ወደመሆን ይሸጋገራል። በዚህም ሳቢያ ደግሞ በተገቢው መልኩ የአገልግሎት ግዜ ሲያበቃ በሂደት የመተካካት ፣ ለተተኪው ስልጣንን ማሳለፍ ወይም መልቀቅ የሚለው መሰረታዊ የዲሞክራሲና የሃገር እድገት መርህ ይጣስና ስልጣንና ሹመት የቤተሰብና የዘመድ አዝማድ የኑሮ ምሰሶ ሆኖ ስለሃገር እድገት ማሰብ በራስ ወዳድነትና በግለኛ የማይጠረቃ ፍላጎት ይተካና ስልጣን ወይም ሹመት ላይ እስከወዲያኛው ሙጭጭ ማለትን ያመጣል።
በቅርቡ የተካሄደው የኢህአዴግ ስብሰባ  “ . .  የፓርቲያችን ዋናው ችግር ሙስናና አድር ባይነት ነው ስለዚህ . . . “
የሚቀጥለው የኢህአዴግ ስብሰባ “ . . . . ባለፈው ያልናችሁ ዋናዎቹ ችግሮቻችን ሙስናና አድርባይነትን የምንዋጋበትን እቅድ በአፋጣኝ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ እናወጣለን  . . . . .”
እኔ በዚህች ላብቃ  . . . . . መስናና ዘረፋው ግን አምሮበት እንደቀጠለ ነው።
natnaelkab@gmail.com


Tuesday, March 11, 2014

In the name of democracy, landgrab and genocide in Ethiopia

By Nebiyou Alemayehu & Natnael kabtimer (oslo)
March 10, 2014


On 6th March 2014 Frontline club Oslo organized an event in collaboration with NEW FRONTIERS entitled “In the Name of Democracy: Land Grabbing and Genocide in Ethiopia” at Filmen Hus Oslo. As it is known Norway is the only Western country that has signed a bilateral agreement with the Ethiopian intelligence service facilitating forced return of refugees, even if the Ethiopian dictatorial government always receives strong international criticism for its gross human rights violations. In the event, four different individuals from similar and different point of view about Ethiopia and Ethiopians have been invited to present their standpoint about the current Ethiopian regime.

Abdullahi Hussein was the president’s adviser and head of the Ogaden TV channel Cakaara News. He had responded to the abuses and atrocities against civilians and for a few years he copied the president’s secret video files. Files included the internal meetings where individual officers and soldiers in the regional militia testify arbitrary arrests, torture, murder, extortion and rape. He presented unique video documentation revealing the dictatorship’s harsh treatment of its opposition, which he has smuggled out of the government and is taking to the International Criminal Court in The Hague. In general he has presented about the horrific circumstances in the Ogaden region, the handling of the evidence, and the process towards the International Criminal Court in The Hague.
The other presenter was Mr Obang Metho. He is a human rights activist who has tirelessly advocated for human rights, justice, freedom and environment, enhanced accountability in politics and peace in Africa for over 10 years. He has briefed leaders and officials at United Nations, the European Parliament, the US Department of State, the US Senate, the US House of Representatives, the World Bank and the Council for Foreign Relations, amongst others. From Norway, Artist Solveig Syversen, who works with Ethiopian refugee status in Norway, has presented her work-in-progress documentary about the Norwegian-Ethiopian agreement of returning refugees.

The fourth person who presented his opinion about the current Ethiopian regime was, One Norwegian researcher from Bergen . His presentation was different from the other three in many ways and he seems to have a close relationship with the current Ethiopian regime. He presented verbal presentation in favor of the current Ethiopian regime specifically about the development of Ethiopia by referring the regime’s problems presented by Mr Hussien and Mr Metho as an “Exception”. His whole presentation has created great deal of disappointment in the audiences. He left at the middle of the event by avoiding questions from audiences.

Saturday, March 1, 2014

ሕወሀትና የኢዮጵያዊነት ገጽታው

በናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ)
 
ናትናኤል ካብቲመር
ባለፈው የካቲት 11 2006 የህወሃት ምስረታ በአል ሲከበር /ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ያደረጉትን ንግግር ሲጀምሩ የትግራይ ሀዝብ ከአስከፊው ብሄራዊ ጭቆናና ፋሽስታዊ ስርአት ጋር ተናንቀው ……. ብለው ነበር እናም በርግጥ የህወሀት የትግል መስመር እና አለማ ምን ነበር? አሁን እንደሚባለው ኢትዮጵያን ከአስከፊው የደርግ ስርዐት ለመታደግ ወይስ በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ እነደተናገሩትየድህነት ጠበቃ የነበረውን ደርግአሸንፎ ብልጽግና ለማምጣት?
ሕወሐት የተመሰረተበትን አላማ የሚገልጽ የህወሀት ማኒፌስቶ ( 1968 የታተመ መጸሔት) ለዚህ ጥሩ መልስ አለው ሰነዱ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አጠቃላይ የህወሀት አላማ እና መድረሻየጨቋኟ አማራ ብኄርንጭቆና ለማስወገድ እና የትግራይ ሪፓብሊክ ማቋቋም ነው፡፡ ስለኢትዮጵያ እድገትም ሆነ የወደፊት አላማ ያስቀመጠው የልማት እቅድ ሳይሆን  የኢትየጵያን አንድነት በሚያፈራርሱ ዘረኛ አስተሳሰብ የታጨቀ ነው፡፡ ለዚህም ይመሰላል ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር የሚለውን ዘወትር በሸገር ራዲዮ የምንሰማውንና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚወደውን አባባል የጎሪጥ የሚመለከቱት ብዙ የነበሩት፡፡ ስለዚህም የህዝቡን ስሜት ከዚህ ለማስለወጥ ብዙ ነገሮቸ ተብለዋል፡፡ ለምሳሌ የዚሁ ስርአት አጫፋሪ በሆነው ኢትዮ ቻናል  በተባለው ጋዜጣ ላይ (እትሙን አላስታውሰውም) ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር የሚለውን ክቡር ቃል አጅግ ተራ በሆነ አቀራረብ ምንም ነገር ለዘላለም አይኖርም ስለዚህ ይህ አባባል ስህተት ነው የሚል ትርጉም ሰጥቶ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳውን  ይዞ ብቅ ያለው፡፡ በነራችን ላይ ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕታት የሚሉንም እነሱው ናቸው አናም ዘላለም የሚለው ቃል ትርጉም ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ጠባቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር ስለሆነ ነው  ፡፡ 
አሁን ጠዋት ማታ የሚያደነቁረን የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ የሚነግረን የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጠው ኢህአዴግ ያመጣው  የዘር ፖለቲካ በነሱ አገላላጽየብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ሲረጋጋጥመሆኑን ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ተረጋግጧል በሚሉት በዚህ ዘመን የትግራይ ተወላጅ (የህወሃት አባል) መሆን ብቻ ሁሉም በሮች እንዲከፈቱለት የሚያደርግ ልዩ የይለፍ ካርድ መሆኑን የምናየው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ እዚህ ላይ ሁል ጊዜ የሚያስገርመኝን አንድ ማሳያ ላስቀምጥ፤ ብዙ የትግርኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ሰዎች (በተለይም የስርአቱ አጫፋሪዎች)ንግግር ሲኖር ወይም ትንሽ ጭቅጭቅ ሲኖር ልክ የትግራይ ተወላጆች እነደሚሉት ዋእ! ዋእ! ሲሉ እንሰማለን፡፡ ዘወትር ፈገግ ቢያሰኘኝም ለኔ የዚህ ትርጉሙ ብዙ ነው በጣም ብዙ።፡፡
እንደምናስታውሰው ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስለ ሀገር ፍቅር የሚናገሩ ነገሮች በሙሉ በመንግስት ሚዲያዎቸ በአዋጅ የተከለከሉ ይመስል አስከ ቅርብ አመታት ድረስ መስማት ብርቅ ነበር፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያዊነትን ከህዝቡ አእምሮ ለመነጠል በስውር አንዳንዴም በግልጽ የሚደረጉ ግፊቶች ነበሩ፡፡ አሁንም በተለይ ለዚህ ዘመን ትውልዶች ሀገራችን የረጀም ግዜ አኩሪ ታሪከ እንዳላት ሳይሆን ተራ የሆነ የዘር ፖለቲካ እንደ አኩሪ ታሪክ ይማራሉ፡፡ የሃገራችን ህፃናት ማንታቸውን ረስተው የፈረንጅ ቋንቋ የሚናገሩ ሆነው እየተቀረጹ ነው፡፡ በሃገራቸው ቋንቋ አንድ ዓረፍተ ነገር ተናግሮ መጨረስ ሲተናነቃቸው እያስተዋልን ነው። አንድ ሰው 12 አመት መሉ ተምሮ እንግሊዝኛ መናገር የዕውቀት ጣሪያ እስኪመስል ድረስ ዛሬ በሀገራችን በተለይም በአዲስ አበባ የልጆች የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንግሊዝኛ መሆን ከጀመረ ቆይቷል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በክልሎች አካባቢ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህረተ ከመሰጠቱ ጋር ተያይዞ (በነገራችን ላይ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር በራሱ ችግር የለውም) እነዚህ ተማሪዎች ሌሎች ቋንቋዎችን  በተለይም አማርኛን እንዲጠሉ በመደረጋቸው የሀገራቸውን ብሄራዊ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ዜጎች ማየት ጀምረናል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጰያ አንድነቷ ተከብሮ የኖረው በልጆቸዋ ውድ መስዋትነተ እንደሆነ ማወቅ ማንነትን ማወቅ እንጂ የብሄር ጭቆና ማስታወስ አይደለም በነገራችን ላይ ኢትዮጵየዊነትን ከአማራ ብሄርተኝነት ጋር ማገናኘት አንዱ የህወሃት አስገራሚ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ ሁሉም ማወቅ ያለበት ግን ህወሃትም ሆነ እርሱ የሚመራው ኢህአዴግ ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጰያዊያንን በዘር ከመከፋፈል ውጭ ሰለሀራችን ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ሁለንተናዊ አድገት የማይጨነቅ መሆኑን ነው፡፡ስለዚህ እኛ ኢትዮጰያዊያን ፀረ ኢትዮጰያ አቋም ያለውን አስከፊ ስርዐት ማስወገድና ልጆቻችንን ታላቅ ሀገር እንዳላቸው ማስተማር  ለነገ ብለን የማናሳድረው ሀላፊነት ይመስለኛል፡፡
ኢትዮጲዊነት ያሸንፋል!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!